The Latest from AABE

የህዝብ ጥቅም ላለባቸው (PIEs) ተቋማት ኦዲት ለማከናወን ለተመሰከረላቸው ኦዲተሮች የተሰጠው የሽግግር ጊዜ ለ6 ወራት ተራዘመ

የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ (AABE) የዳይሬክተሮች ቦርድ ባካሄደው 25ኛ መደበኛ ጉባዔ፣ ለህዝብ ጥቅም ላለባቸው (Public Interest Entities – PIEs) ሪፖርት አቅራቢ ተቋማት የሚሰጠውን የኦዲት አገልግሎት በተመለከተ የሽግግር ውሳኔ አሳልፏል።
በመመሪያ ቁጥር 1096/2017 መሠረት ለእነዚህ ተቋማት የኦዲት አገልግሎት ፐብሊክ ኦዲተሮች ብቻ እንዲሰጡ የተደነገገ ቢሆንም፣ ቦርዱ ለሽግግር ወቅት ባስተላለፈው ውሳኔ መሠረት ካለው ፐብሊክ ኦዲተር ቁጥር አንጻር የተመሰከረላቸው ኦዲተሮች በ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት ብቻ የኦዲት አገልግሎት እንዲሰጡ ወስኗል።
ከዚህ የሽግግር ጊዜ በኋላ ለህዝብ ጥቅም ላለባቸው ተቋማት በተመሰከረላቸው ኦዲተሮች የሚሰጥ የኦዲት አገልግሎት ተቀባይነት እንደማይኖረው ቦርዱ ገልጿል።

News