The Latest from AABE

የIFRS S1 እና S2 የዘላቂነት ሪፖርት ስታንዳርዶች የትግበራ ፍኖተ-ካርታ ፀደቀ

የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ (AABE) የዳይሬክተሮች ቦርድ ባካሄደው 25ኛ መደበኛ ጉባዔ፣ የIFRS S1 እና IFRS S2 የዘላቂነት ሪፖርት ስታንዳርዶች የትግበራ ፍኖተ-ካርታን በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።
ውሳኔው መንግሥት በ2027 በሚካሄደው COP32 ዝግጅት እና የGreen Taxonomy ትግበራ ጋር ተጣጥሞ፣ የፋይናንስ ዘርፉ ጤናማ፣ ግልጽ እና ዘላቂ እንዲሆን የሚያግዝ አስፈላጊ እርምጃ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤
በተፈቀደው ፍኖተ-ካርታ መሠረት፣ ትግበራው አቅም ካላቸው ከፍተኛ የህዝብ ጥቅም ሪፖርት አቅራቢ አካላትን መነሻ በማድረግ እንደሚጀምር፣ በዚህም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ እና በፈቃደኝነት መተግበር የሚፈልጉ ሌሎች ተቋማት በደረጃ ይካተታሉ ተብሏል።
በመሆኑም የዳይሬክተሮች ቦርዱ ትግበራው ውጤታማ እንዲሆን የአቅም ግንባታ ሥራዎች በተደራጀና በተቀናጀ መልኩ እንዲከናወኑ በመወሰን፣ የትግበራ ፍኖተ-ካርታው በጥብቅ ዲሲፕሊን እንዲተገበር አፅድቋል።

News