The Latest from AABE

የኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ ከተመሠከረላቸው የሂሳብ ባለሙያዎች ኢንስቲትዩት እና የሂሳብ እና ኦዲት ሙያ ማህበራት ጋር በመተባበር ከአዲስ አበባ 903 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምትገኘው በአማራ ክልል በሰሜን ጎንደር ዞን አዳርቃይ ወረዳ በ 02 ቀበሌ በመገኘት የክረምት የበጎ ፈቃድ መርሃ ግብር ን አከናውኗል። ነሃሴ 14/2018 ዓ.ም.

የቦርዱ ም/ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ጽዋዬ ሙሉነህ በመንግስት በተቀመጠ አቅጣጫ መሠረት እንደቦርድ የክረምት በጎ ተግባራት ስራዎችን በወረዳው ለማከናወን እንደተገኙ በመግለጽ፣ በዚህም ቦርዱ ለትውልድ ግንባታ መሠረት ከመጣል አንጻር ያለው ሚና የጎላ በመሆኑ የመዋዕለ ህጻናት ትም/ቤት ግንባታን ለማከናወን መወሰኑን ገልጸዋል።

ከመዋዕለ ህጻናት ግንባታ ማስጀመሪያ መርሀ ግብር ጎን ለጎን ለ100 ተማሪዎች የደብተር፣የቦርሳ፣የላጲስ፣የሶፍት፣የሳሙና፣የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ፣እርሳስ፣መቅረጫ ፣ እስኪሪፕቶ የመሳሰሉት ቁሳቁሶች ድጋፍ ተደርጓል።

በመርሀ ገብሩ በአዲስ መልክ እድሳት የተደረገለትን የፋሲል ግንብ(ፋሲለደስን) ለመጎብኘት ተችሏል።