የቦርዱ ም/ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ጽዋዬ ሙሉነህ በመንግስት በተቀመጠ አቅጣጫ መሠረት እንደቦርድ የክረምት በጎ ተግባራት ስራዎችን በወረዳው ለማከናወን እንደተገኙ በመግለጽ፣ በዚህም ቦርዱ ለትውልድ ግንባታ መሠረት ከመጣል አንጻር ያለው ሚና የጎላ በመሆኑ የመዋዕለ ህጻናት ትም/ቤት ግንባታን ለማከናወን መወሰኑን ገልጸዋል።
ከመዋዕለ ህጻናት ግንባታ ማስጀመሪያ መርሀ ግብር ጎን ለጎን ለ100 ተማሪዎች የደብተር፣የቦርሳ፣የላጲስ፣የሶፍት፣የሳሙና፣የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ፣እርሳስ፣መቅረጫ ፣ እስኪሪፕቶ የመሳሰሉት ቁሳቁሶች ድጋፍ ተደርጓል።
በመርሀ ገብሩ በአዲስ መልክ እድሳት የተደረገለትን የፋሲል ግንብ(ፋሲለደስን) ለመጎብኘት ተችሏል።






