The Latest from AABE

የአካውንቲንግ ቴክኒሺያን የብቃት ትግበራን (ATQ) የተመለከተ የምክክር መድረክ ተካሄደ

ሚያዚያ 06/2017ዓ.ም. አዲስ አበባ፣

የገንዘብ ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ የሒሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ ከዓለም ባንክ ጋር በመተባበር የአካውንቲንግ ቴክኒሽያን የብቃት ትግበራን (ATQ) የተመለከተ የምክክር መድረክ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተካሂዷል፡፡

በመድረኩም በዋነኝነት ዓለም አቀፉን የአካውንቲንግ ቴክኒሺያንን ብቃቶች መነሻ በማድረግ አገር አቀፍ የታክስ እና የፐብሊክ ሴክተር ቴክኒሺያን ብቃቶች ፕሮግራም ሞጁሎችና ሲለበስ እንዲሁም ረቂቅ የትግበራ ፍኖታ ካርታ ቀርቦ ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

በመድረኩ ተሳታፊ የሆኑ ባለድርሻ አካላትም በቀረቡት ሰነዶች ላይ የተለያዩ ግብዓት ሊሆኑ የሚችሉ ጥያቄዎችና አስተያየቶችን አንስተው ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡