The Latest from AABE

የፋይናንስ ሪፖርት ግምገማ ቁልፍ ግኝቶች እና ጥራትና ተአማኒነት ላለው የፋይናንስ ሪፖርት የጋራ ተጠያቂነት ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ ተካሄደ

የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ የፋይናንስ ሪፖርት ግምገማ ቁልፍ ግኝቶችንና ተዓማኒ የፋይናንስ ሪፖርት አቀራረብን ለማረጋገጥ የጋራ ተጠያቂነት በሚሉ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ ከማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ኃላፊዎች ጋር ህዳር 9 ቀን 2019 ዓ.ም. በግራንድ ኤሊያና ሆቴል አካሂዷል።

በመድረኩ የፋይናንስ ሪፖርት ግምገማ ቁልፍ ግኝቶች እንዲሁም የስራ አመራር(ማኔጅመንት)፣ የቦርድ አባላት፣ ኦዲተሮችና ተቆጣጣሪ አካላት በተዓማኒ የፋይናንስ ሪፖርት አቀራረብ ሂደት ያላቸው ሚናና ኃላፊነት ላይ ገለጻዎች ቀርበዋል።

News

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 8 ቀን 2019 ዓ.ም፡- የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ (AABE) ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት አቀራረብ ደረጃን (Full IFRS) በሚተገብሩ ተቋማት ላይ ሲያከናውን የቆየውን የፋይናንስ ሪፖርት ግምገማ (Financial Report Review – FRR) ቁልፍ ግኝቶችና የቁጥጥር ማሻሻያ እርምጃዎችን የተመለከተ የምክክር መድረክ በግራንድ ኤሊያና ሆቴል አካሂዷል።