የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ የፋይናንስ ሪፖርት ግምገማ ቁልፍ ግኝቶችንና ተዓማኒ የፋይናንስ ሪፖርት አቀራረብን ለማረጋገጥ የጋራ ተጠያቂነት በሚሉ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ ከማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ኃላፊዎች ጋር ህዳር 9 ቀን 2019 ዓ.ም. በግራንድ ኤሊያና ሆቴል አካሂዷል።
በመድረኩ የፋይናንስ ሪፖርት ግምገማ ቁልፍ ግኝቶች እንዲሁም የስራ አመራር(ማኔጅመንት)፣ የቦርድ አባላት፣ ኦዲተሮችና ተቆጣጣሪ አካላት በተዓማኒ የፋይናንስ ሪፖርት አቀራረብ ሂደት ያላቸው ሚናና ኃላፊነት ላይ ገለጻዎች ቀርበዋል።









