



ጥቅምት 19/2019 ዓ.ም፣ በገንዘብ ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት የ1ኛ ሩብ ዓመት የአፈጻጸም ሪፖርት በተገመገመበት ውይይት፣ የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ዋና ዳይሬክተር አቶ ውብሸት ታደለ የቦርዱን የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት አቅርበዋል።
በሪፖርቱ የቦርዱ ዋና ዋና የሥራ አቅጣጫዎችና የተከናወኑ ተግባራት የቀረቡ ሲሆን ፤ በቀጣይ የቦርዱ ትኩረት የተቋማዊ ሪፎርምንና የሰው ኃይል ስትራቴጂን ማጠናከር፣ በፋይናንስ ሪፖርቶችና በኦዲት ድርጅቶች ላይ የጥራት ማረጋገጫ ሥራዎችን ማስቀጠል፣ የሕግ ተጠያቂነትን ማረጋገጥ፣ የሂሳብ መግለጫዎችን በዲጂታል ሥርዓት የማቅረብ አሠራርን ማሳደግ እና ከባለድርሻ አካላት ጋር ያለውን ትብብር ማጠናከር ላይ እንደሚሆን ተገልጿል።
እነዚህ የቀጣይ አቅጣጫዎች የሂሳብና የኦዲት ሙያውን ጥራት፣ የፋይናንስ ሪፖርት ተዓማኒነትና የተቋሙን የቁጥጥር አቅም ለማጠናከር የሚያግዙ ዋና ዋና የሥራ አቅጣጫዎች መሆናቸው ተመላክቷል።