(22/12/2016 አዲስ አበባ)፡ – የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ በ21/12/2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ኢንተርሌክዠሪ ሆቴል “በINPAG (International Non-Profit Accounting Guidance Exposure Draft 3)” ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተካሄደ።
ውይይቱን በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር የከፈቱት የቦርዱ ም/ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ጽዋዬ ሙሉነህ በንግግራቸው ተሳታፊዎች በሙያቸው ለትግበራው መሳካት የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በፋይናንስ ኦዲት እና ማረጋገጥ ደረጃዎች እና ኮርፖሬት ገቨርናንስ መሪ ሥራ አስፈፃሚ የተዘጋጀው ይህ ውይይት ዓላማውን “በINPAG ED 3 ዙሪያ Non-profit organizations (NPOs) ከቦርዱ ቴክኒካል አማካሪዎች እና ከተመሰከረላቸው ኦዲተሮች ጋር የጋራ መግባባትን በመፍጠር በትግበራው ላይ የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ለማስቻል ሲሆን ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች፣ የኦዲት ባለሙያዎች፣ የሂሳብ ባለሙያዎች እና ሌሎች ተሳታፊዎች የተገኙበትን ይህን ውይይት የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል አቶ ጌትነት ኃይሌ በተሳካ ሁኔታ መርተዋል።
እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ዓለም አቀፍ ደርጃውን የጠበቀ ሪፖርት ማቅረቢያ አሰራር ባለመኖሩ ምክንያት ወጥነት ያለው ሪፖርት (General purpose financial report) ለሪፖርቱ ተጠቃሚዎች ማቅረብ እንዲቻል ተብሎ ለትርፍ ላልተቋቋሙ ድርጅቶች የተዘጋጀው ይህ ውይይት በመጨረሻም ከተሳታፊዎች በተነሱ ሃሳብና አስተያየቶች ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።