የኢትዮጵያ የሒሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት፣ የቦርዱ የስራ ኃላፊዎች እና መላው ሠራተኞች እንዲሁም የሙያው አካላት፤ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን፣ ገዜ ጎፋ ወረዳ፣ የኪንቾ ቀበሌ በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ ህይወታቸውን ላጡ ወገኖች የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን እየገለፁ፣ ለሟች ቤተሰቦች፣ ወዳጅ ዘመዶች፣ ለክልሉ ማህበረሰብ እና ሀዘኑ ለተጋባባቸው ኢትዮጵያውያን ወገኖች መፅናናትን ይመኛሉ፡፡