The Latest from AABE

የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ሰራተኞች በማህበራዊ ተሳትፎ

መስከረም 26 ቀን 2017 ዓ.ም. አዲስ አበባ፡ –  በገዛኸኝ ጋሞ

”እኔ ደም በመለገስ የእናቶችን ሞት እቀንሳለሁ” በሚል መሪ ቃል የቦርዱ የሴቶች ህጻናትና ወጣቶች አካቶ ትግበራ ከህዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ ጋር በጋራ ያዘጋጁት የደም ልገሳ መርሃ ግብር የቦርዱን የአመራር አካላትና ሰራተኞችን በማሳተፍ በ23/01/2017ዓ.ም በቦርዱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ የተካሄደ ሲሆን የቦርዱ ሰራተኞች ደም በመለገስ ለወገን ደራሽነታቸውን በተግባር አሳይተዋል።

በዚህ በጎ ፍቃድ አገልግሎት ላይ ከብሄራዊ የደም ባንክ አገልግሎት የመጡ ባለሙያዎች ባስተላለፉት መልዕክት ”በኢትዮጵያ በዓመት 300,000 ዩኒት (ከረጢት) ደም ያስፈልጋል፡፡ ይህንን ፍላጎት ለማሳካት በየዓመቱ ከ3 እስከ 4 ጊዜ የሚለግሱ 1000 ያህል በጎ ፈቃደኛ መደበኛ ደም ለጋሾች ያስፈልጋሉ፡፡” ያሉ ሲሆን በቦርዱ የሴቶች ህጻናትና ወጣቶች አካቶ ትግበራ ባለሙያ የሆኑት ወ/ሪት አና መለሰ በበኩላቸው በአሁኑ ጊዜ እንደ ሃገር ደም የመለገስ ባህላችን ካለበት ውስንነት በመነጨ በተለያዩ የህክምና መስጫ ተቋማት ውስጥ ቁጥሩ ቀላል የማይባል ህይወት በደም እጦት ምክንያት እያለፈ ይገኛል ብለዋል። ወ/ሪት አና መለሰ አያይዘውም ደም በመለገስ ክቡር የሆነውን የሰው ልጆች ህይወት መታደግና እናቶችን ማዳን ትውልድን ማስቀጠል ነው ብለዋል፡፡