The Latest from AABE

ሚዲያ የህዝብተጠቃሚነትንለማረጋገጥያለውንተፅዕኖየማስረዳት ኃይል የሚኖረው የህዝብ ተዓማኒነት ማግኘት ሲችል እንደሆነ ተጠቆመ

14 ነሐሴ 2017 ዓ-ም፣ አዳማ ፡ – የኢትዮጵያ የሒሣብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ ከመንግስት እና ከግል ሚዲያ ተቋማት ለተውጣጡ የሚዲያ ባለሙያዎች የቦርዱን ስትራቴጂ የማስተዋወቅያ የጋራ የምክክር መድረክ አካሂደ፡፡

በዕለቱም የቦርዱ ም/ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ጽዋዬ ሙሉነህ የመድረኩ አስፈላጊነት የቦርዱን ዓላማዎች ተደራሽ ለማድረግ የሚዲያ ሚና ጉልህ እንደሆነ ለማስረዳት ነው ብለዋል፡፡

አገራችን እየተገበረች በምትገኘው በማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙ ትልልቅ ስኬቶችን እያስመዘገበች የምትገኝ ሲሆን በተለይ ኢትዮጵያ ኢኮኖሚዋን ለዓለም ገበያ እየከፈተች ባለችበት በአሁኑ ወቅት የአካውንተንሲ ሙያ ብሔራዊ ጥቅምን ከማስከበር እና የህዝብ ተጠቃሚነትን ከማረጋገጥ አኳያ ያለውን አዎንታዊ እና አሉታዊ ተፅዕኖ ለማስረዳት ሚዲያ ትልቅ አቅም እንዳለው ተገልጿል፡፡  

ቦርዱ በየጊዜው ተለዋዋጭ በሆነው አለም ውስጥ ኮሙዩኒኬሽን በተቋማት እና በተገልጋይ መካከል ሁሉን አቀፍ መግባባትን ለመፍጠር፣ የሙያውን ጉልህ ሚና ከተጠቃሚው ተደራሽ ለማድረግ እና ከወቅቱ ጋር ለመራመድ ወሳኝ ሚና እንዳለው በማመን ዓላማ ተኮር በሆነና ሊለካ በሚችል መልኩ በተቀናጀና በተናበበ አግባብ አጠናክሮ ለመምራትና ለመተግበር እንዲቻል ከኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ጋር በጋራ በመሆን የኮሙኒኬሽን ስትራቴጂ አዘጋጅቷል፡፡

ኮሙኒኬሽን በአንድ ጉዳይ ላይ ልዩነት የመፍጠር አቅም እንዳለውና ለሚዲያውም የሚቀሰም አበባ ተምሳሌት እንደሆነ በመግለጽ ያለጠንካራ ኮሙኒኬሽን ለአንድ ዓላማ የቆመ ማህበረሰብ መፍጠር እንደማይቻል፤ እንዲሁም  የህዝብ ተጠቃሚነትን ከማረጋገጥ አኳያ ያለውን አዎንታዊ እና አሉታዊ ተፅዕኖ ለማስረዳት ሚዲያ ትልቅ ኃይል አለው ሲባል የጋራ ትርክቶች ላይ ሲሰራና የህዝብን ተአማኒነት ማግኘት ሲችል እንደሆነ ስትራቴጂውን ያቀረቡት የዘርፉ ምሁር  ጌታቸው ድንቁ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

ተሳታፊዎችም ቦርዱ የኮሙኒኬሽን ስራ በስትራቴጂያዊ መልኩ መመራት እንዳለበት በማመን ከባለድርሻ አካላት ጋር የመመካከሪያ መድረክ ማዘጋጀቱን በጥንካሬ አንስተዋል፡፡

በመጨረሻም የቦርዱ ተ/ዋና ዳይሬክተር አቶ ፍቃዱ አጎናፍር በመዝጊያ ንግግራቸው እንደተናገሩት በኢትዮጵያ የአካውንተንሲ ሙያ የሚጠበቅበትን ውጤት ለማስመዝገብ እንዲቻል ባለሙያውን የሚያፈራ እና የሚያበቃ የኢትዮጵያ የተመሰከረላቸው የሂሳብ ባለሙያዎች ኢንስቲትዩት ወደሥራ መግባቱን አውስተው ከሚዲያ አካላት ጋር በጋራ ሊያሰራ የሚችል የሚዲያ ፎረም እንደሚፈጠር ተናግረዋል፡፡