The Latest from AABE

የኢትዮጵያ የተመሠከረላቸው የሂሳብ ባለሙያዎች ኢንስቲትዩት

በሒሳብ አያያዝ ፤ፋይናንስ እና ኦዲት ያለውን የሰለጠኑ የተመሰከረላቸው የሒሳብ ባለሙያዎች ለማፍራት እና ሙያውን ለማሳደግ የኢትዮጵያ የተመሠከረላቸው የሂሳብ ባለሙያዎች ኢንስቲትዩት በአዋጅ ቁጥር 1372/2017 ተቋቁሟል፡፡ ይህን ተከትሎም ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፤ የአጋር ድርጅቶች፤ የሙያ ባለቤቶች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበትም ታህሣሥ 2 ቀን 2018 ዓ.ም. የስራ ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር በይፋ ተካሄዷል፡፡የኢንስቲትዩቱ ዋና ዓላማ ለሥራ ዝግጁ የሆኑ ብቃት ያላቸው የተመሠከረላቸው የሒሣብ ባለሙያዎችን በብዛት እና በጥራት ማፍራት ሲሆን፣ከሚሰጣቸው የትምህርት ዘርፎች አንዱ የሆነውን የሂሳብ አያያዝ ቴክኒካል ብቃት (Accounting Technician Qualification-ATQ) ስልጠና ለመስጠት ምዝገባ በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ ስልጠናው በመካከለኛ ደረጃ ያለዉን የባለሙያ እጥረት ይቀርፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ስልጠናዉ ክህሎትን መሰረት ያደረገና ተማሪዎች ባሉበት ሆነው መከታተል የሚችሉት ነው፡፡ኢንስቲትዩቱ ተማሪዎችን ለፈተና ለማዘጋጀት በአዲስ አበባ እና በክልሎች ካሉ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እና የስለጠና ድርጅቶች ጋር አብሮ ይሰራል፡፡ማንኛዉም ፍላጎት ያላቸው በኢንስቲትዩቱ ድረ-ገጽ (https://www.eticpa.et/) ላይ የተገለፀውን መስፈርት የሚያሟሉ አመልካቾች በድረ-ገጹ ላይ በመግባት መመዝገብ የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች በመደወል፣ኢሜል አካውንት መጠቀም ወይም በአካል በመገኘት መጠየቅ ይቻላል፡፡ስልክ: (+251) 111540900/04/ ድረ-ገጽ፡https://www.eticpa.et/ ኢሜል: info@eticpa.et ማዳጋስካር ጎዳና፣ 6 ኪሎ፣ ከግብፅ ኤምባሲ ፊት ለፊት፣ ሊደርሺፕ ኢንስቲትዩት ህንፃ፣ 3ኛ ፎቅ