The Latest from AABE

በተሻሻለው መመሪያ ቁጥር 1096/2017 ላይ ሥልጠና ተሰጠ

የኢትዮዽያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ በተሻሻለው የሂሳብ እና ኦዲት ሙያ ፍቃድ አሰጣጥ እና የሒሣብ ሙያ ማኅበራት ምዝገባ መመሪያ ቁጥር 1096/2017 ላይ ለሚመለከታቸው ሠራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ::


ስልጠናውን የሰጡት የቦርዱ የህግ አገልግሎት ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሰለሞን ነጋሽ እንደተናገሩት ቀድሞ የነበረው የሂሳብ እና ኦዲት ሙያ ፍቃድ አሰጣጥ እና የሒሣብ ሙያ ማኅበራት ምዝገባ መመሪያ ቁጥር 805/2013 ላይ ማሻሻያ ማድረግ በማስፈለጉ እና የተሻሻለው መመሪያ ቁጥር 1096/2017 በርካታ ማሻሻያዎች እና አዳዲስ አገልግሎቶችም የተካተቱበት መሆኑን ገልፀዋል።
በዚሁ መሠረት አገልግሎቱን የሚሰጡ ሠራተኞች ስለህጉ እና ህጉን ተከትሎ መስተካከል በሚገባቸው የአሠራር ሥርዓቶች ላይ አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት ለማድረግ ህጉን ጠንቅቆ መረዳት ያስፈልጋል ብለዋል።


በግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው ላይ የተሳተፉት ሠራተኞች በመመሪያው ላይ ሰፋ ያለ ውይይት እና የተግባር ሙከራዎች ያደረጉ ሲሆን በቀጣይ ህጉን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችሉ ግብዓቶችን የማዘጋጀት፣ በተለይ አገልግሎቶቹ በቴክኖሎጂ የሚታገዙ በመሆኑ ማሻሻያ የማያስፈልጋቸው ዘርፎች ላይም ግንዛቤ መያዛቸውን ተናግረዋል።
በመጨረሻም የቦርዱ ተ/ዋና ዳይሬክተር አቶ ፍቃዱ አጎናፍር ቦርዱ በሚሰጠው አገልግሎት በሚያደርጋቸው ማሻሻያዎች ላይ በቂ ዝግጅት ማድረግ የሚያስፈልግ መሆኑን አሳስበዋል።