The Latest from AABE

የኢትዮጵያ የተመሰከረላቸው የሒሣብ ባለሙያዎች ኢንስቲትዩት ዓላማ

የኢትዮጵያ የተመሰከረላቸው የሒሣብ ባለሙያዎች ኢንስቲትዩት በኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መጋቢት 04 ቀን 2017 ዓ.ም በማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1372/2017 መጽደቁ ይታወሳል፡፡

በሀገራችን በመንግስት እና በግሉ ዘርፍ ዓለም ዓቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት ደረጃዎች ትግበራ የሚያስፈፅሙ በቂ እና ብቁ የተመሰከረላቸው የሐሧብ ባለሙያዎችን በማፍራት የሒሣብ ሙያን እና የባለሙያውን አቅም በማሳደግ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ሙያውን እና ባለመያውን የሚወክል የህዝብ ጥቅምን የሚያስጠብቅ ተቋም በማስፈለጉ ኢንስቲትዩቱን ማቋቋም አስፈልጓል፡፡

የኢትዮጵያ የተመሰከረላቸው የሒሣብ ባለሙያዎች ኢንስቲትዩት የሐሣብ ሙያን ማሳደግ እና ቀጣይነቱን ማረጋገጥ፣ የሒሣብ ሙያ የሕዝብን ጥቅም ማስጠበቁን ማረጋገጥ፣ የሒሣብ ባለሙያዎች የላቀ ዕውቀት፣ ክህሎት፣ ሥነ-ምግባር እና የአሠራር ደረጃ እንዲኖራቸው በማድረግ የሒሣብ ሙያ በህዝብ ዘንድ ተዓማኒነት እና ዕውቅና እንዲያገኝ ማድረግ፣ በሀገር ውስጥ እና በዓለም ዓቀፍ ደረጃ እውቅና የሚኖራቸው ብቁ እና በቂ ባለሙያዎችን ማፍራት እና የሒሣብ ባለሙዎችን የሙያ ነጸነት ማስከበር ቀዳሚ ዓላማዎቹ ናቸው፡፡

አዋጁ ሚያዝያ 20 ቀን 2017 ዓ.ም. በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ገበያ ላይ ውሏል፡፡