የኢትዮጵያ የሐሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ የ2017 በጀት ዓመት የመጀመረያ ሩብ ዓመት አፈፃፀምን ከአጠቃላይ ሠራተኛ ጋር ጥቅምት 18 ቀን 2017 ዓ.ም. ገመገመ፡፡
ውይይቱን የቦርዱ ተ/ዋና ዳይሬክተር አቶ ፍቃዱ አጎናፍር የመሩት ሲሆን የበጀት ዓመቱ ዕቅድ የአሥር ዓመቱ ስትራቴጂያዊ ዕቅድ እና የሦስት ዓመቱ መካከለኛ ዘመን ዕቅድን መሰረት ማድረጉን አቶ ፍቃዱ አውስተው የሥራ ክፍሎች እና አመራሩም ካደረጉት ግምገማ በተጨማሪ እንደአጠቃላይ የተከናወኑ እና ያልተከናወኑ ተግባራትን፣ ያጋጠሙ ችግሮች እና ቀጣይ አቅጣጫዎችን የጋራ ማድረግ እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል፡፡
የአፈፃፀም ሪፖርቱን የስትራቴጂክ ጉዳዮች ሥራ አስፈፃሚ አቶ ተሾመ ደሳለኝ ያቀረቡ ሲሆን የዕቅድ አፈፃፀሙ ሶስት ዋና ዋና ዓላማዎች እና አስራ አምስት ግቦችን መያዙን እና የሩብ ዓመቱ አፈፃፀምም 87 ከመቶ መከናወኑን አቅርበዋል፡፡
በዕለቱም ብቃት እና ልምድ ያለው የሰው ሃይል እጥረት፣ በሙያው ላይ የተለያዩ አገር በቀልና አለም ዓቀፍ ተሞክሮዎችን በልምድ ልውውጥ አለማዳበር እና የተጠናከረ የአቅም ግንባታ ሥራዎች አለመከናወን እንደችግር ተነስተው ውይይት ተካሂዶባቸዋል፡፡
በተመሳሳይም የቦርዱ የአስተዳደር እና አገልግሎት አሰጣጥ ሪፎርም ስራ አፈፃፀም በተጠናከረ ሁኔታ እየተካሄደ መሆኑም ተገምግàል፡፡
በመጨረሻም ሁሉም የሥራ ክፍሎች በመጀመሪያው ሩብ ዓመት ያልተከናወኑ ተግባራትን በቀጣይ ለማጠናቀቅ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እና በመተባበር ማከናወን እንደሚገባ አቅጣጫ የተሰጠ ሲሆን የፋይናንሻል ሪፖርት ግምገማ እና የኦዲት ጥራት ማረጋገጥ ምርመራ ተግባራት ከተያዘው ዕቅድ አንፃር አመርቂ ውጤት የተመዘገበባቸው እና ውጤቱንም ይፋ በማድረግ አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ፣ እንዲሁም የሂሳብ ሙያ ድርጅቶች ላይ የተካሄደው የክትትል፣ ቁጥጥር እና ድጋፍ ሥራ አስተማሪ ከመሆኑም አልፎ ሙያው የህዝብን ጥቅም ማስጠበቁን እና ህገ-ወጥ ተግባራትን በማጋለጥ በፋይናንስ ሥርዓቱ እና በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ሊያስከትል የሚችለውን አሉታዊ ተፅዕኖ ሁሉም ለሙያው ስነ-ምግባር ተገዢ ሆኖ ሊከላከል እንደሚገባ ተገልጿል፡፡