(ነሐሴ 19 ቀን 2016 ዓ.ም. አዲስ አበባ)፡ የኢትዮጵያ የሒሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ አመራሮች እና ሠራተኞች “የምትተክል ሀገር የሚያጸና ትውልድ” በሚል መሪ ሃሳብ በአንድ ጀምበር ስድስት መቶ ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል ፕሮግራምን መሰረት በማድረግ ከገንዘብ ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ ከተማ ልዩ ስሙ ሐያት መቄዶኒያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነሀሴ 17 ቀን 2016 ዓ.ም. አሻራቸውን አኑረዋል፡፡
በዕለቱም የገንዘብ ሚኒስትር ሚኒስቴር ዴኤታ እና የቦርዱ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ ፕሮግራሙ ላይ በመገኘት አሻራቸውን ያኖሩ ሲሆን ሀገራችን ላለፉት ተከታታይ ስድስት ዓመታት እያከናወነች ባለው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ተፈጥሮን በማዳን ሁነኛ አስተዋፅኦ ማበርከቷን ያስታወሱ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ሪፖርት አቅራቢ አካላት ቢዝነሳቸውን በሚያከናውኑበት ወቅት ተቋማዊ እና የአየር ንብረት ለውጥ ዘለቄታዊነትን በሒሳብ መግለጫዎቻቸው አካትተው ማቅረብ የሚያስችል ስታንዳርድ (IFRS S1 & S2, Sustainability-related risks and opportunity disclosure standards) ማውጣታቸው ኢትዮጵያ ለጉዳዩ ያላትን ፅኑ አቋም ማሳያ ነው ብለዋል፡፡
የቦርዱ ም/ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ጽዋዬ ሙሉነህ በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው አሻራቸውን ባሳረፉበት ወቅትም እንደተናገሩት በያዝነው ዓመት በጎንደር እና በጅማ ከተሞች በገንዘብ ሞኒስቴር አስተባባሪነት በተካሄደው የችግኝ ተከላ ፕሮግራም የቦርዱ ሰራተኞች የተሳተፉ መሆናቸውን ገልፀው በመላው ሀገራቲ በሚከናወነው በአንድ ጀምበር የ600 ሚሊዮን ችግኝ መትከል መርኃ-ግብር ልዩ ቦታ የሚሰጠው መሆኑን ተናግረዋል፡፡