The Latest from AABE

በ2016 የኦዲት ጥራት ግምገማ አፈጻጸም እና የቀጣይ እቅዶች ላይ ውይይት ተደረገ።

አዲስ አበባ፡- የኢትዮጵያ የሒሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ የሒሳብ ሪፖርትና የኦዲት ጥራት ማረጋገጫ ሥራ አስፈፃሚ ሠራተኞችና የቴክኒክ አማካሪዎች የ2016 በ.ዓ. የፋይናንስ ሪፖርት እና የኦዲት ጥራት ማረጋገጥ አፈጻጸም እና የ2017 እቅዶች ላይ ተወያዩ።

በሀገሪቱ ከፍተኛ የኦዲት ጥራት ደረጃዎችን ማስከበር ያለውን ወሳኝ አስፈላጊነት አጽንኦት የሰጡት ተ/ዋና ዳሬክተሩ አቶ ፍቃዱ አጎናፍር እንደተናገሩት “በፋይናንስ ሪፖርት አቀራረብ ስርዓታችን ላይ ህዝባዊ አመኔታን ማስቀጠል ከሁሉም በላይ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው” ብለዋል። “የስራ ክፍሉ ዋነኛ ዓላማ የኦዲት ጥራትን ለማረጋገጥ የኦዲት ድርጅቶች ሙያዊ ደረጃዎችን እንዲያከብሩ እና አስተማማኝ ኦዲቶችን ለተጠቃሚዎች ማለትም እንደ ባለሀብቶች፣ ባለአክሲዮኖች ፣ አበዳሪዎች፣ ተቆጣጣሪዎች እና ፖሊሲ አውጭዎች እና በአጠቃላይ ህብረተሰብ ዘንድ አስተማማኝ ኦዲቶችን ማቅረብ ነው” ሲሉ አክለዋል።

የሥራ ክፍሉ የስራ አስፈፃሚ አቶ አህመድ መሀመድ የ2016 የኦዲት ጥራት ግምገማ መርሃ ግብሩን አጠቃላይ በኦዲት ድርጅቶች የሚደረጉ የኦዲት ስራዎችን በማካተት አቅርበዋል። ግምገማው በርካታ ማሻሻያ የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮችን ለይቷል፣ የሰነድ አሰራሮች፣ የስጋት ግምገማ ሂደቶች፣ የጥራት ቁጥጥር ስርዓቶች፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች፣ የውስጥ የጥራት ግምገማ ሁኔታ እና የአቅም ችግሮችን ከአጭር፣ የመካከለኛ እና ረዥም ጊዜ ሁኔታን ያማከለ መፍትሔም ጭምር አቅርበዋል።

ወደ 2017 በ.ዓ. በመሸጋገር ቡድኑ ተለይተው የታወቁትን ጉድለቶች ለመቅረፍ ለምሳሌ ለኦዲተሮች የተሻለ ስልጠና እና ለሰራተኞች ባለሙያዎች ምርጥ ተሞክሮ/ልምድ የሚያገኙበት፣ አጠቃላይ የድርጅቶችን ተግዳሮቶች እንዴት መፍታት እንደሚቻል ፣ የጥራት ቁጥጥር ፖሊሲዎችን ማሻሻል እና የክትትል ዘዴዎችን ማጠናከር፣ በተጨማሪም፣ ቡድኑ የኦዲት ጥራት ምርመራ ፕሮግራሙን ወሰን በማስፋት ሁሉንም የኦዲት ድርጅቶችን ለመሸፈን የሚያስችሉ መንገዶችን ፈትሿል።

በመጨረሻም ዋና ዳይሬክተሩ ሲያጠቃልሉ “የ2017 እቅድ የፋይናንሺያል ሥራችንን አስተማማኝነት እና ግልጽነትን ከፍ ለማድረግ ከባለፈው አመት የተወሰዱ ትምህርቶችን በማጠናከር ለሀገራዊ ኢኮኖሚው መሻሻል እንደ ገፊ ምክንያትሆነው ለመጡ ውስጣዊ እና ውጫዊ ሁኔታዎች በቂ ምላሽ ለመስጠት ተገቢው ትኩረት ተሰጥቶ ይሰራል” ብለዋል።