የትራንስፖርትና ሎጀስቲክ ሚኒስቴር በሚሊኒየም አዳራሽ ባዘጋጀውና ትኩረቱን <<በመንገድ ደህንነት>> ላይ ባደረገው አለም አቀፍ ኤክስፖ ላይ የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ሠራተኞች የተካተቱበት የጋራ ጉብኝት ተካሄደ፡፡
ከሰኔ 26/2016 ዓ.ም ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ቀናት በሚቆየው በአውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪ ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ኤክስፖ ላይ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችና ተጠሪ ተቋማት ሰራተኞች ተሳታፊ የሆኑ ሲሆኑ በዛሬው የጉብኝት መርሃ-ግብር የገንዘብ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት ሠራተኞች ተሳታፊ ሆነውበታል፡፡
በኤክስፖው ላይ የመንገድ ደህንነትን ሊያረጋግጡ የሚችሉ ዘርፈ ብዙ ቴክኖሎጂዎችና የፈጠራ ውጤቶች ለዕይታ የቀረቡ ሲሆን ጎብኚዎችም በተመለከቱት ነገርና በዘርፉ እንደ ሃገር እየተሰራ ባለው ስራ መደሰታቸውን ገልጸዋል፡፡
