re

የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ በአለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀትና አቀራረብ ደረጃዎች አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 01/2012 ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር መስከረም 15 ቀን 2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ሳፋየር ሆቴል የግማሽ ቀን ውይይት አደረገ፡፡

በውይይቱም ቦርዱ ቀድሞ ባወጣው የትግበራ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ደረጃዎቹን የተገበሩ እና በትግበራ ሂደት የገቡትም ሆነ እየገቡ ያሉ በሁሉም መስክ ያሉ የህዝብ ጥቅም ያለባቸውና ሌሎችን ጨምሮ ካሉ ተቋማት የተወጣጡ 120 የድርጅት ባለቤቶችና ስራ አስኪያጀች ተሳትፈዋል።

መድረኩን የመሩት የቦርዱ ጊዜያዊ አስተባባሪ አቶ ደመምላሽ ደበሌ እንደተናገሩት ከፍተኛ ጥራት ያለው የፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀትና አቀራረብ ደረጃዎች ትግበራን በሀገራችን እውን ለማድረግ የወጣውን አዋጅና ደንብ ለአፈጻጸም ያመች ዘንድ በሂሳብ ሙያ ስለመሰማራት የሪፖርት አቅራቢ አካላት የሚል መመሪያ ቁጥር01/2012 አውጥቶ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ተወያይቶ በሚመለከተው አካል ለማጽደቅ እየሰራ መሆኑንና በየደረጃው ያሉ ሪፖርት አቅራቢ አካላትም የፋይናንስ ሪፖርታቸውን አዘጋጅተው በሚያቀርቡበት ጊዜ መከተል ያለባቸውን አቅጣጫ የሚያሳይ መመሪያ ላይ በመወያየት ገንቢ አስተያየተቸውን በማበርከት መመሪያውን የጋራ ማድረግ እንደሚያስፈልግ አብራርተዋል፡፡

በተመሳሳይም አቶ ወርቁ አዲስ የቦርዱ የህግ ማስከበር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የመወያያ ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን በተለይ ሪፖርት አቅራቢ አካላት ስለአዋጅና ደንቡ የህግ ማዓቀፎች ጽንስ ሃሳብ ግንዛቤ እንዲኖራቸው አጠር ያለ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን በቀጣይ በመመሪያው የሪፖርት አቅራቢ አካላትን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ገለጻ አድርገው ውይይት ተካሂደበታል፡፡

በመጨረሻም የውይይቱ ተሳታፊ ሪፖርት አቅራቢ አካላት ቦርዱ ስለደራጃዎቹ ግንዛቤ ለማስጨበጥ እየሰራቸው ያሉ ተግባራት የሚያሰመሰግኑና ተጠናክረው መቀጠል ያለባቸውንና መመሪያውም ከመጽደቁ በፊት በየደረጃው ያሉ ባለድርሻ አካላት እንዲወያዩበት መደረጉ ተገቢ መሆኑን ተናግረዋል፡፡