director-general

ክብርት ወ/ሮ ሂክመት አብደላ አብዱልመሊክ ከጥቅምት 20 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድን በዋና ዳይሬክተርነት እንዲመሩ በኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር በክቡር ዶ/ር ዐብይ አህመድ በተጻፈ ደብዳቤ ተመደቡ፡፡

ክብርት ዋና ዳይሬክተሯ ጥቅምት 24 ቀን 2012 ዓ.ም. ከቦርዱ የሥራ ኃላፊዎች ጋር የሥራ ትውውቅ ባደረጉበት ወቅት የሀገሪቱን የፋይናንስ ሥርዓት ጤናማነት በማረጋገጥ የድርጅቶችን የውድቀትና ኪሳራ ስጋት ለመቀነስ ቦርዱ የተሰጠውን ከፍተኛ ተልዕኮ ለማሳካት ከመላው የድርጅቱ ሰራተኞችና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡

አዲሷ ዋና ዳይሬክተር የተመደቡት ቦርዱ በህግ ከተቋቋመበት 2008 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሐምሌ 10 ቀን 2011 ዓ.ም በዋና ዳይሬክተርነት ሲመሩ የነበሩት አቶ ጋሼ የማነ ደስታ በፈቃዳቸው መልቀቃቸውን ተከትሎ ሲሆን ላለፋት ሶስት ወራት የዋና ዳይሬክተሩ አማካሪ እና የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ደምመላሽ ደበሌ ተረዳ ቦርዱን በጊዜያዊ አስተባባሪነት ሲመሩ ቆይተዋል፡፡