The Latest from AABE

የኢትዮጵያ የተመሰከረላቸው የሂሳብ ባለሙያዎች ኢንስቲትዩት መስራች አባላት የመጀመሪያው ዙር ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 16 ቀን 2018 ዓ.ም.  የኢትዮጵያ የተመሰከረላቸው የሂሳብ ባለሙያዎች ኢንስቲትዩት መስራች አባላት የመጀመሪያው ዙር ውይይት በአዲስ አበባ ከተማ ግራንድ ኤሊያና ሆቴል ተካሂደ፡፡

የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ተ/ዋና ዳይሬክተር እና የኢንስቲትዩቱ ጊዜያዊ አስተዳደር ም/ቤት ሰብሳቢ አቶ ፍቃዱ አጎናፍር  በመክፈቻ ንግግራቸው እንደተናገሩት የውይይቱ ዓላማ ኢንስቲትዩቱ በአዋጅ 1372/2017 ተቋቁሞ እና ጊዜያዊ የአስተዳደር ምክር ቤት ሰባት አባላት ተመድበውለት ሥራ ከጀመሩ ወዲህ ኢንስቲትዩቱን ወደ ስራ ለማስገባት በርካታ ተግባራት የተከናወኑ መሆኑን ገልፀው ኢንስቲትዩቱ የIFAC አባል ለመሆን በሚያደርገው ጉዞ በመስራች አካላት የሚከናወኑ ተግባራት ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡ ጉዳዮች በመኖራቸው ነው ብለዋል፡፡

በውይይት መድርኩም በዋናነት ኢንስቲትዩቱ የተቋቋመበት አዋጅ እና አሁን በምን ሂደት ላይ እንደሚገኝ እንዲሁም የቀጣይ ተግባራት ላይ በአቶ ሰለሞን ነጋሽ የቦርዱ የህግ ሥራ አስፈፃሚ እና በአቶ ደረጀ ገላና የኢንስቲትዩቱ ጊ/የፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ ገለጻ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

መስራች አባላቱ የዚህ ታሪክ አካል መሆንን እንደትልቅ እድለኝነት በመውሰድ እንደአገር ከሙያው ጋር ተያይዞ በርካታ ያሉብንን ችግሮች ለመቅረፍ መፍጠን እንደሚያስፈልግና ኢንስቲትዩቱም በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና እንዲኖረው መስራት እንደሚጠበቅባችው አቶ ፍቃዱ አሳስበዋል፡፡

የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው እንደ አገር ኢንስቲትዩቱ በመቋቋሙና መስራች አባል በመሆናችው እጅግ ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

አክለውም ኢንስቲትዩቱ በአለም አቀፍ ደረጃ እውቅና እንዲያገኝ ከመስራት ጎን ለጎን እንደ አገር ለኢትዮጵያ ገበያ በፍጥነት መድረስ እንደሚገባ እና ዓለም ዓቀፍ ተዋናይ በመሆን ሀገራዊ ክብር እና የህዝብን ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ አንፃር በቁጭት መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡