The Latest from AABE

የኢትዮጵያ የተመሠከረላቸው የሒሳብ  ባለሙያዎች ኢንስቲትዩት  ሚና    

አዲስ አበባ፡ – መጋቢት 14 ቀን 2017 ዓ.ም.  የሂሳብ አያያዝ ሙያ (The Accountancy Profession) የፋይናንስ ሪፖርት ጥራትን ለማሻሻል እና በተለይ በግሉ ሴክተር ውስጥ ግልፅነትን ለማጎልበት ወሳኝ ሚና ይጫወታል። ሙያው ዓለም ዓቀፍ የቢዝነስ ቋንቋ እንደመሆኑ ለኢኮኖሚ እድገት በጣም ወሳኝ ለሆኑት ለድርጅት አስተዳደር (Corporate Governance) መሻሻል፣ ለኢኮኖሚ ተቋማት ቅልጥፍና፣ ለፋይናንስ ሴክተሩ መረጋጋት እና ለሀገር ተወዳዳሪነት አስተዋፅኦ ያደርጋል። የሂሳብ አያያዝ ለኩባንያዎች እውነተኛ መገለጫ ዋነኛው የተግባቦት ዘዴ ሲሆን፣ የአንድን ሀገር ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ የእድገት ደረጃን በማሳየትም የጎላ ሚና አለው።  እንዲሁም እንደ የማህበራዊ እና የማክሮ ኢኮኖሚ መለኪያ መሳሪያ ተደርጎ የሚቆጠር ሲሆን ይህም ለኢኮኖሚ ልማት ስኬት እንደ ቅድመ-ሁኔታም ይሆናል።

በተጨማሪም የመንግስትን የፋይናንስ አስተዳደር ግልፅነት እና ተጠያቂነትን ለማሻሻል፣የአገልግሎት አሰጣጥና የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማጎልበት ተሳታፊዎች እንዲሁም በመንግስት ዘርፍ ያሉ ባለድርሻ አካላት የበለጠ እንዲተባበሩ ይጠበቃል።


የሂሳብ ሙያ በአፍሪካ የእድገት ታሪክ ውስጥ ወሳኝ ሚና የሚጫወት ሲሆን አፍሪካ በቅርብ ዓመታት ውስጥ በኢኮኖሚም ሆነ በሂሳብ አያያዝ ረገድ አስደናቂ እድገት እና ጽናትን አሳይታለች። በአለም አቀፍ ኢኮኖሚ ውስጥ እያደገ የመጣው ተፅእኖ እና የንግድ ስራዎቿ እንደ አለምአቀፍ የንግድ ሀሳብ ይበልጥ ማራኪ እና ኢንቨስትመንት በመሳብም በሂደት ለውጦች እያሳየች ትገኛለች። ለዚህም ፕሮፌሽናል የሂሳብ ባለሙያዎች የአህጉሪቱ አቅምን ለመገንባት እና የካፒታል ገበያን ለማዳበር፣ ግልጽነትን እና የድርጅት አስተዳደርን የሚያጎለብት የፋይናንስ ሪፖርት አቀራረብ እና አዘገጃጀት ጥራትን ለማሻሻል ብዙ መስራታቻው ይገለፃል።

ለዚህ አህጉራዊ የዘርፉ አስተዋፅዖ የኢትዮጵያ አበርክቶ በታሪክ እዚህ ግባ የሚባል አለመሆኑ ቢቆጭም በዘመን አጋጣሚ ሙያውን ማሳደግ እና ብሄራዊ ጥቅም ማስጠበቁን ለማረጋገጥ በመጠንም በጥራትምየተሟላ ባለሙያ ለማፍራት የኢትዮጵያ የተመሰከረላቸው የሂሳብ ባለሙያዎች ኢንስቲትዩት (ETICPA) ድርሻውን ለመወጣት መፍትሔ ይዞ መጥቷል፡፡